የነብዩ ቅዱስ ሔኖክ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ሄኖክ

by Solomon ZeEthiopia


Lifestyle

free



የቅዱስ ሔኖክ የዘመን አቆጣጠር መሰረቱ መጽሃፍ ቅዱሳዊ መሆኑን በመጸሃፈ ኩፋሌና ሄኖክ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ነው። በዚህ ዘመን አቆጣጠር መሰረት መጋቢት ቀዳሚ ወር ነው፡፡ አንድ ሙሉ አመት ሁሌም 364 ቀናቶች( 364/7 = 52 ያለቀሪ ሱባኤ ወይም ሳምንት) እንዲሁም 12 ወራቶች ሲኖሩት እያንዳንዳቸው 30 ቀናትን ይዘዋል። በየሶስት ወሩ ደግሞ አራቱ ወቅታትን የሚለዩ አራት የመለያ(መባቻ) ቀናት አሉ። እነዚህ የመለያ ቀናት ሁሌም ቅዳሜ ላይ የሚውሉ ሲሆኑ በግንቦት 30ና በሰኔ 1 መካከል በነሃሴ 30ና በመስከረም 1 መካከል በህዳር 30ና በታህሳስ 1 መካከል በየካቲት 30ና በመጋቢት 1 መካከል ያሉ ቀናት ናቸው።አመቱ 364 ቀናት (52 ሳምንታት ብቻ) ስላሉት በአላት አጹዋማት ሁሌም ቀናቸዉን ሳይለውጡ ጸንተው ይኖራሉ። ለምሳሌ ጥንተ ብርሃነ ልደቱ ታህሳስ 17 ማክሰኞ ላይ ከዋለ ሁሌም በየአመቱ ታህሳስ 17 ማክሰኞ ይውላል። ይህ ደግሞ ብርሃነ ትንሳኤውን ሁሌም በጥንተ ቀኑ ሚያዚያ 13 እሁድ እንዲከበር አመች አርጎታል። ባህረ ሃሳቡ ጥንተ ቀመሩ (ዘመን መቁጠር የጀመረበት) ማክሰኞ ስለሆነ ዘመነ ሔኖክ ይህ ስእተት በመሆኑ ከእሁድ በመጀመሩ የባህረ ሃሳቡ ማክሰኞ ለዘመነ ሔኖክ እሁድ ይሆናል።